የቆንጆዋ ወጣት መስኖይ (ግጥም)

ይህ ግጥም/ዘፈን ከመስኖይ ዘውግ ይመደባል፤ መስኖይ የጥንት የሐረሪ ሕብረተሰብ ዘፈን ነው1፡፡ የተጻፈው በሐረሪ አጀም ነው – ቋንቋው ሐረሪ ሲሆን ፊደሉ ግን ዓረብኛ ነው፡፡ ይህ ግጥም በጽሑፍ የተገለበጠው በ18ኛ ክፍለ ዘመን መግቢያ ሲሆን ቋንቋውም አንዳንድ ቦታ ለአማርኛ በጣም ይቀርባል፡፡ ለምሳሌ ሁለተኛው ስንኝ መጨረሻ ላይ የሐረሪው ጽሑፍ ራሱ ጠባይሽ ዕንዴትዋ ይላል፡፡

 ኮኸን    336 

عينش جل جل * درم قلط يمسن باقيلا

عينشم عينينا * درم قلط طبايش عنديتوا

عينشم بال وكا * درم قلط وكبش حلنكا

وخاي نا زروا * درم قلط انكويي ويزروي

وخاي قلم سر * يدحنال عالم يمسل

 وخاي وردنا * جد عالم سوال افات نجدين

ትርጉም

አይንሽ  አንጸባራቂ፣  ወጣት ቆንጆ፣ (ይመስል) የመስኖ ባቄላ

አይንሽማ አይኔ ነው፣ ወጣት ቆንጆ፣ ጸባይሽ እንዴትዋ

አይንሽ ባለ ዋጋ፣ ወጣት ቆንጆ፣ ወገብሽ አለንጋ

የሽመል አበባ፣ ወጣት ቆንጆ፣ እንኮይ ወይዘሮ

የኔ ሽመል የመቃ ስር፣ ዓለም ያድን ይመስል

የኔ ሽመል ጽጌረዳ፣ ቤትሽ ከይፋት ነጋዴ የተዋዋለ…


  1. አብዱራህማን መሐመድ ገጽ 37፡፡ አብዱልሐሚድ አብዱላሂ ቃሉ የመጣው ከዓረብኛ መስነዊይ እና ትርጉሙም መንቶ (ባለ ሁለት ስንኝ ግጥም) እንደሆነ ጽፏል (አብዱልሐሚድ አብዱላሂ ገጽ ፡፡ ↩︎

Leave a comment

Create a free website or blog at WordPress.com.

Up ↑