ቼ 282
ይህ ባለ አራት ስንኝ የዓረብኛ ግጥም የሐረርን ከተማ ውበት ያወሳል፡፡ የከተማዋም ታላቅነት የተመሰረተው በቅዱሳኖቿ በአሚር ኑር ቢን ሙጀሃዲን እና ሼክ አባድር ጥበቃና በአዋቂዎቿ ብርሃን እንደሆነ ይናገራል፡፡ የግጥሙ ዜማ ልክ በዓረብኛ ጠዊል1 የሚሉት ነው፡፡
فمدينة الحرر تزهو بلاوليا * ولا سيما حقا بامام الابرار
يحق لها ان ترخي اذيال ثوبها * لان عامرها مبيد للكفار
ولم لا وامام المجاهدين فيها * وبرقوعها نور العلماء الاخيار
ومن اربع الجهات تجري انهارها * ولاكن حاميها الامام ابادر
የሐረር ከተማ በቅዱሳኖቿ ታንጸባርቃለች፣ በተለይም በጻድቃኑ ኢማም
የቀሚሷን ዘርፍ ትሰበስብ ዘንድ ይገባል፣ እሷን የገነባ ካፊሮችን ደምስሷልና
እንዴታ፣ የሙጃሂዱን ኢማም እዚያ ነውና፣የፊቷም ሽፋን የዓዋቂዎቿ ብርሃን
ወንዞቿ ከአራቱም አቅጣጫ ይፈሳሉ፣ ጠባቂዋም ኢማም አባድር ነው
- ጠዊል (በአማርኛ ረጅም) በአረብኛ ግጥሞች በብዛት የሚታየው የዜማ ልክ ዓይነት ነው፡፡ በአንድ ስንኝ (መስመር) ሁለት 14፣ 14 ቀለሞች የያዙ ሐረጎች አሉት (በአጠቀላይ 28 ቀለሞች)፡፡ አንዳንዱ ቀለም ሲያጥር (ለምሳሌ በ)፣ ሌላው ይረዝማል (ለምሳሌ ቢ)፡፡ ↩︎
Leave a comment