እራሱ ለተሰበረ

የሐዲስ መጽሐፈ ፈውስ ገጽ 182፤ ቢኤል 828ቅ.73

ለአካላት ሁሉ እራሱ ለተሰበረ ተፈረስም ላይ ለወደቀ ተበቅሎም ለወደቀ እራሱም ላበጠ ለተገመሰ ላልተገመሰም ላላበጠም ደምም ታፉ ታፍንጫው ተዓይኑ ተጆሮው ላልፈሰሰው እንዴህ አድርገው ይፈውሱት

አስቀድመህ እራሱን ላጨው

የስንዴ[1] ፍትግ አሰር[2] የደቀቀ ዶቄት እስኪ ሆን ፍጨው

የባቄላ[3] ዶቄት

የምስር[4] ዶቄት

የድምብላል[5] ፍሬ

የአንስላል[6] ፍሬ

የጥድ[7] ፍሬ

፲ቅንጣት የናትራን[8] ቅጠል ወቅጠህ አፍላው ሁሉንም በጠና ጠጅ እሁሉ እስኪ ለወስ

ኋላ ግን ቅብዓ ኑግ[9] ዱልበት ነጭ ሰምም ጨምርበት እፍራንም[10] ዱልበት

እየለወስህ አፍላው በእንጨት ቀጭን አይሁን

እራሱን ኋላም አንገቱን ቀባው እወሰን እጠጉሩ ዠምሮ ታላቅ አጥንቱ ካለ ድረስ አንገቱ ወሰን ድረስ ቀባው

ቅባኑግ የዶሮ ስብ በየቀኑ እጁንም እግሩንም እሸው

አቈልቊለህ አቈልቊለህ በጥኑ ታልታመመ ደም አውጣለት ተወገቡ በዋገምት ወይም ተክንዱ ደም አውጣለት መድኃኒቱን አድርግለት ለእራሱ በጎ ነው ፍቱን ነው፡፡


[1] የብር እኽል፤ የሳይንስ ስሙ Triticum sativum ነው፡፡ ደስታ 1191፤ ወልደ ሚካኤል 176

[2] ገለባው፤ የገብስም ዐሻሮ ገለባ ዐሠር ይባላል፡፡ ደስታ 946

[3] ያበባ እኽል፤ የሳይንስ ስሙ Vicia sativa ነው፡፡ ደስታ 188፤ ወልደ ሚካኤል 117

[4] በውስጡ ብረታዊ ባሕርይ ያለበት ያበባ እኽል፤ የሳይንስ ስሙ Lens culinaris ነው፡፡ ደስታ 823፤ ወልደ ሚካኤል 164

[5] ክብ ታናሽ ቅመም፤ የሳይንስ ስሙ Coriandrum sativum ነው፡፡ ደስታ 332፤ ወልደ ሚካእል 128

[6] እንስላል የሚባለው እንጨተ ቀጪን ተክል፤ የሳይንስ ስሙ Pimpinella anisum ነው፡፡ ደስታ 1177፤ ወልደ ሚካኤል 146

[7] እንጨቱ ልዝብ የሆነ፣ ለቤት ሕንጻ የሚስማማ ዛፍ፡፡ የሳይንስ ስሙ Juniperus procera ነው፡፡ ደስታ 542፤ ወልደ ሚካኤል 181

[8] የአሪቲ ወገን ሳይሆን አልቀረም [Artemisia absinthium]፡፡ ንግሥት 2000 ገጽ 71

[9] ከጥቁር የቅባት እኽል የሚገኝ ዘይት፤ የቅመሙ የሳይንስ ስም Guizotia abyssinica ነው፡፡ ደስታ 837፤ ወልደ ሚካኤል 1997፣ 167

[10] የዛፍራን አበባም ይሉታል፡፡ ቀይ የአበባ አይነት ሆኖ ከውስጡ የሚገኘው ቃጫ መሳይ ቅጥይ ለቅመም፣ ለማለያም (ልብስ ለማቅለም) ያገለግላል፡፡ [Croccus sativus] ደስታ 133፣ ዳባዲ 590

Leave a comment

Create a free website or blog at WordPress.com.

Up ↑