ጤናዳም

ጤናዳም/ ፄና አዳም        

Ruta chalepensis

ተክሉ

ጤናዳም ከኢትዮጵያ እንደተገኘ ወይም መልማት ከጀመረ ብዙ ዘመን እንዳለፈው አጥኚዎች ይናገራሉ። በ5/6ኛ ክፍለ ዘመን የግእዝ ጽሑፍ ስሙን ጼናታም ይሏል። ከባሕር ወለል ከ1500 እስከ 2500 ሜትር ከፍታ ባለው ምድር ወቅት ሳይለይ ይበቅላል፤ ረግረግ ያልሆነ ምድር ሁሉ ጭንጫውም እንኳ ይስማማዋል። ቁመቱ ባብዛኛው አጭር ቢሆንም እስከ ሶሶት ክንድ ሊረዝም ይችላል። ወደ ሰማያዊ የሚያደላው ቧሔ ቅጠሉ ከጣት አንጓ የሚያናንስ ሆኖ እንደ አጽቆቹ እየተፈራረቀ ይወጣል።  ብጫ አበባዎቹ 4/5 ቆበቶች አላቸው። ባለ አራት ፍልቅልቅ የፍሬ ራሶቹ በስል ቂንዶች የታቀፈ ነው፤ በውስጣቸው አምስት እስከ አሥር ጥቃቅን ሕጉሮች (ቅንጣቶች) ይይዛሉ። ችግኙ ከንቅሉም፣ ከሕጉሩም ይፈላል።

ጥቅም

ለሙቅ መጠጦች ማጣፈጫ፣ ለወተት ተዋጽኦና ላንዳንድ የመብል ስንድቶች ቅመም ነው። “እርጥበት እንደ ሙቀት ለበዛበት ሰው ፄና አዳም ደቁሰህ አጠጣው ወይም ቅጸሉን ይብላ” ይላል ያ18ኛ ክፍለ ዘመን የመድኃኒት ጽሑፍ፤ በዚያን ጊዜ ሕክምና የሚያድነው ጠባይ በማስተካከል እንደሆነ ስለሚታሰብ የጤናዳም ጠባይ ትኩስና ደረቅ በመባሉ ለባለ ላበት ትኩሳት መፍትሔ ሆኖ ነው። ለሆድና ለጥርስ ሕመምም ማስታገሻ ይሆን ነበር።

ሥርወ ቃል

የጤናዳም ዘውግ ጼናዳም/ጤናዳም የሚለው ቃል የሽታ አመልካች የሆነውን “ጼን” ባዕድ አድርጎ፣ ደስ የሚያሰኝ ተብሎ የሚተረጎመውን “አዳም” አጣምሮ የተመሠረተ ነው። ባዕዱ ከከፊቾው ሲን c underscore dot እና ከሳሆው ሲን “ሽታ”፣ ከናኦው ሲንኡስ ” አፍንጫ”፣ ከግእዙ ጼነወ ” መዓዛ ሰጠ” እና ዐጠነ፣ ከአካዲው ኤጼኑ ” ማሽተት”፣ ከአማርኛው ሽነት ይዛመዳል፤ ከኖስራታዊ የቋንቋ ቤት *ሻን/ሳን “አፍንጫ፣ ስሜት”፣ በቅርብም ከአፍረእስያ የቋንቋ ቤት  * ሲን “ሽታ” ከሚሉት ዘሮች የወጣ ነው። የዚህን ባዕድ መነሻ ከሌሎች ፊደላት እያወራረሱ የሚነገሩ የዕጽዋት አይነቶች ሽቱነት ስላለቸው ለማዕጠንት፣ ለመጣፍጥነት ይፈለጋሉ :- ጼና-ዳም (Ruta chalepensis)፣ ጥን-ጁት (Otostegia integrifolia) ፣ ጠን-በለል (Jasminum abyssinicum)፣ ሰን-ሰል (Justicia schimperiana) ይባላሉ።  ለባር-ስነት “ባሕር ሽነት” (Myrtus communis) አንጻር የሆነው ሽነ-ት (Myrica salicifolia) እና ዕጣን (Boswellia) ለዚህ ዘውግ ስሞች መነሻ ዘሮች ሳይሆኑ አልቀሩም። እኒህ ባለ ማዕዛ ዕጽዋት በሳይንስ ሁለት ወገን ናቸው:- 1)አምስት ቆበቶቻቸው ስለሚጋጠሙ አበባቸው የማይበተንና ቅጠሎቻቸው ተጋጥመው የሚሠርጹ (Asteridae Lamiales) 2)ቆበቶቻቸው የሚበተኑ፣ በአባቢነታቸው የሚታወቁ (Rosidae)።

ኤንግልስና ወረደ 123. ንግሥት 163. ያንሴን 104-110 …ስዕል ካስፈለገ የ107 ጥሩ ነው። Or 828, 147v። ሉቃስ 11.42።hamito semitic dictionary 442  cin (underscore dot)1865, sansun “smell” 2199, sin 2251። ቦምሐርድ 238-239

Leave a comment

Create a free website or blog at WordPress.com.

Up ↑