ሉቅዬ (አማርኛ)፤ ፈሰሰት (ትግርኛ)
Terpsiphone viridis (የሳይንስ ስም)
መልክ
ደረተ ነጭ፣ ዠርባቸው ቀይ ከለድማ፣ ቁንጯቸው ዝርዝር፣ ባለ ክበብ ዓይን አካለ ትንሽ ወፎች፤…. ቁመታቸው ከመንቆር እስከ ዥራት ጫፍ….ያኽላል። ወንዱ በክንፉ ጠርዝ ነጭ የጣለበት ሆኖ ከዥራቱ የሚቀጠሉ ረዥም ነጭ ላባዎች አሉት።

መብል
በራሪ ሕዋሳት
ትዳር (ኑሮ)
በጣም በረሃ ከሆኑ አከባቢዎች በስተቀር በመላ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።በበልግ (መጋቢት-ሰኔ) በባላ መጋጠሚያ ከዕፅዋትና ከድንጋይ ሽበት ጥርኝ የምታኽል ጎጆ (ስፈትዋም ቁመትዋም ወደ 7 ሳንቲማትር የምትሆን) በሸረሪት ድር መርገው ያበጃሉ።

ሁለት ሶስት ጫጩት እንደተፈለፈሉባት በትጋት አንዱ ወላጅ ሲጠብቅ ሌላው ምግብ እያመጣ ለሁለት ሳምንት ያኽል ያሳድጋሉ፤ ጠባቂዋ እናት ከግልገሎችዋ እንዳይጠጉባት ገንትታ ትጮኻለች፣ ለማስፈራራት ዥራትዋንም ትቀስራች። ኋላም በደንብ መብረር እስኪችሉ አላፊ አግዳሚውን እየጮኸች ታባርራለች።
በዞማ ግቢ
ከዋንዛ፣ ከሾላ ዛፎች፣ በየበኩሉ ሲበሩም ይታያሉ። ጎጇቸው በግንቦት 2016 ከመግቢያው በስተግራ ከብሳናው በታች ተቀይሶ ነበር፤ ለቀውት ከወጡ ወራት ቢያልፍም ዝናብ ተቋቁሞ እስከ ነሐሴ መጨረሻ ቆይቷል።
ዝማሬ
በዞማ ግቢ የሚደምቀው ከየካቲት እስከ ሚያዝያ ነው ….
ድምፅ
https://xeno-canto.org/species/Terpsiphone-viridis?dir=0&order=cnt
የሉቅዬ አሰያየም
ጥንት በብዙ የአፍሪቃና እስያ ቋንቋዎች *ሉክ “ወፍ” የሚል ትርጉም እንደነበረው አጥኚዎች ገምተዋል። ከአማርኛው ሉቅዬ በተጨማሪ በኛ ቋንቋዎች በሶማልኛ ሉኪ፣ በኦሮሚኛ ሉኩ “ዶሮ” ማለት ሲሆን ቢዲያ በሚባልም የቻድ ሀገር ቋንቆ ሉኩኩ የወፍ አይነት ነው።
የወፎች ትልቁ መጽሐፍ ገጽ 543-537፣ የወፎች የትግርኛ ስም…፣አፍሪቃ እስያ ቋንቋ መጽሐፍ ቁ 1685 ገጽ 365
Leave a comment