ጥበብ

በዚህ ክፍል ያሉ ጽሑፎች ስለ ጥበብ የሚናገሩ ወይም በኪን የተሠሩ ሥራዎችን የሚዘግቡ ናቸው፡፡ ጥበብ የሚለው ቃል ትርጕሙ ብዙ ነው፡፡ በብሉይ አንድምታ ከአምላክ የሚገኝ ስጦታ፣ ለሰውነትም ለነፍስም የሚሆን መድኃኒት፣ ዕውቀት ተብሎ ተፈቷል፡፡ ከአንዳንድ ዘንድ ጥበብ ከዕውቀት ቢለይም በሌላ ቦታ ደግሞ ጥበብ እውቀትን፣ ምሳሌን፣ መዝሙርን (ግጥምን) አጠቃሎ ይገኛል፡፡

ይህን የትርጕም ልዩነት በማስተዋል ጥበብን በየመልኩ የሚገልጹ ምንባቦች ተመርጠዋል፡፡ በመጀመሪያው ርእስ ሥነጽሑፍን የሚያስችለው የቀለም ትምሕርት ተገልጽዋል፡፡

ከዚያም የመድኃኒት ሥራ መሠረታዊ ዕውቀት በጥቂቱ ይቀርባል፡፡

በመጨረሻም ያሉት ተውበው ስለሚበጁ ሥራዎች የሚዘክሩ ጽሑፎች ናቸው፡፡

Leave a comment

Create a free website or blog at WordPress.com.

Up ↑